ኬሚካል እና የማዕድን ፍተሻ

የኢተምድ የኬሚካልና የማእድን ፍተሻ ላብራቶር ከ90 በላይ ለሚሆኑ ማእድናት፣ኬሚካሎች እና የመሳሰሉት ምርቶች በ460 የፍተሻ ባህሪያት ላይ የጥራት ፍተሻ ያከናውናል፡፡ እነዚህ ምርቶች በተቀመጠላቸው መስፈርቶች ላይ በተገለጸው መሰረት ለተመረቱበት ዓላማ ስለመዋላቸው፣ ስለደህንነታቸው እና ከሚፈለገው የጥራት ደረጃ መስፈርት አንፃር ይፈተሻሉ፡፡

በኢተምድ የኬሚካል እና የማዕድን ፍተሻ ላቦራቶር የሚፈተሹ ምርቶች እና የፍተሻ ባህሪያት በጥቂቱ

      ምርቶች       

  • የተለያዩ የሳሙና ምርቶች
  • ሲሚንቶ ፣
  • የመዋቢያ ምርቶች፣
  • ቀለም፣
  • ለፅዳት አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካሎች ፣
  • ሃይድሮጂን ፐርኦክሳይድ ፣
  • የተለያዩ ማእድናት
  • ሳኒታይዘር
  • ፋርማሲዩቲካል ምርቶች
  • ጂፕሰም ወዘተ                                                                                                                                                                የፍተሻ ባህሪያት

1.መርዛማ/ጎጂ ማዕድናት/ Heavy Metals

2.አሲዲቲ/ Acidity
3.የምርት ግብዓት አይነት/Ingredients
4.የፀረ-ተባይ ቅሪት/ Pesticide Residue
5.የንፅፅር ፍተሻ/ Comparison test
6. Total fatty matter
7. Concentration ...etc