ኤሌክትሮ ሜካኒካል ፍተሻ ላቦራቶር
የኢተምድ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ላብራቶር የኤሌክትሪካል፣ የሜካኒካል፣ የጨርቃ ጨርቅ፣የቆዳ፣የስቴሽነሪ ምርቶች እና የማሸጊያ ምርቶች ባህርያትን አስመልክቶ ከ70 በላይ የምርት አይነቶች ላይ በ370 ባህርያቶች የፍተሻ ስራን ያከናውናል፡፡
በኤሌክትሮ ሜካኒካል የፍተሻ ላብራቶር ሥር አራት የፍተሻ አገልግሎቶችን የሚሠጡ ላብራቶሮች ይገኛሉ፡፡
እነዚህም ላብራቶሮች
- የኤሌክትሪካል ፍተሻ ላቦራቶር
- የሜካኒካል ፍተሻ ላቦራቶር
- የጨርቃ ጨርቅና የፅህፈት ምርቶች ፍተሻ ላብራቶር
- የቆዳና የማሸጊያ ምርቶች ፍተሻ ላቦራቶር