የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በማር ፍተሻ ዘርፎች ተጨማሪ እውቅናን አገኘ፡፡
መስከረም 27 ቀን 2019ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) ነባር የአክሬዲቴሽን ዘርፎቹን በማስቀጠል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን የላቦራቶሪ ፍተሻ አቅሞች የሚያስፋ ተጨማሪ የአክሬዲቴሽን የምስክር ወረቀት አገኝቷል።
የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ለኢተምድ በማር ውስጥ የሚገኙ 23 የፀረ-ተባይ ኬሚካል ቅሪቶችን እና 3 (heavy metals) ለመፈተሸ የሚያስችለውን የፍተሻ አክሬዲቴሽን ዕውቅና በይፋ ሰጥቶታል። ይህ አዲስ የተገኘ የፍተሻ ዕውቅና ኢተምድ ቀደም ሲል የነበሩትን እንደ ፒኤች (pH)፣ አሲዳማነት፣ የእርጥበት መጠን፣ በውሃ ውስጥ የማይሟሙ ነገሮች፣ የኤሌክትሪክ አስተላላፊነት፣ ሃይድሮክሲሜቲልፈርፉራል (HMF)፣ ግሉኮስ እና ፍሩክቶስ ያሉ መሠረታዊ የማር ጥራት መለኪያዎችን የማረጋገጥ አቅሙን የበለጠ ያጠናክራል።
በዚህ የፍተሻ አገልግሎት ወሰን ማስፋት ሥራ መሠረት፣ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በአሁኑ ወቅት ለማር ናሙናዎች ፍተሻ የሚያገለግሉ 34 እውቅና ባለቤት ሆኗል። ይህም ሀገሪቱ ለማር ጥራትና ደህንነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው አስተማማኝ የምርመራ አገልግሎት ለመስጠት ያላትን አቅም ያሳድጋል። በተጨማሪም አዲሱ ዕውቅና የብሔራዊ የምግብ ደህንነት ሥርዓቱን የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ፣ ጥብቅ የሆኑ የውጭ ገበያ መስፈርቶችን በሀገር ውስጥ ፍተሻ ለማሟላት እና በውጭ ሀገራት ላቦራቶሪዎች ላይ የነበረውን የፍተሻ ጥገኝነት ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።


Related Posts
19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በኢተምድ በድምቀት ተከበረ፡፡
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።