የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢተምድ የመስክ ጉብኝት አደረጉ፡፡

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢተምድ የመስክ ጉብኝት አደረጉ፡፡

ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም

አዲስ አበባ (ኢተምድ)

====================

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የመስክ ጉብኝት አደረጉ፡፡ የሥራ ኃላፊዎቹ በኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ የድርጅቱን ዘመናዊ የፍተሻ ላቦራቶሪዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

 

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ኢተምድ በማዕድን ዘርፍ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተግባር ለመመልከት፣ የምዘና ሂደቶችን፣ የጥራት መስፈርቶችንና የአሠራር ዘዴዎችን ለመረዳት ነው፡፡

 

ከጉብኝቱ በኃላ ኢተምድ በማዕድን ዘርፍ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችና የተስማሚነት ምዘና ሂደቶች፣ የጥራት መስፈርቶችንና የላቦራቶሪ አሠራር ዘዴዎችን እንዲሁም በሁለቱ ተቋማት መካከል ወደፊት ሊኖር በሚችለው የጋራ ትብብር እና የአገልግሎት አጠቃቀም ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡