19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በኢተምድ በድምቀት ተከበረ፡፡

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በኢተምድ በድምቀት ተከበረ፡፡

ጥቅምት 02 ቀን 2019ዓ.ም

አዲስ አበባ (ኢተምድ)

====================      

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) ከጥራት መሠረተ ልማት ተቋማት ጋር በጋራ 19ኛውን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በድምቀት አክብረዋል።

 

የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት፣ ሠንደቅ ዓላማ የጋራ ታሪክ፣ ሉዓላዊነትና የብሔራዊ አንድነት ምልክት መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ቀኑን ስናከብር ሕዝብን ለማገልገል የገባነውን ቃል በማደስና በአገልጋይነት መንፈስ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

 

ዋና ዳይሬክተሯ ቀኑን ልዩ የሚያደርገው የመደመር መንግሥት ምሥረታ በተከናወነበት እንዲሁም አንድነቷን የጠበቀች፣ አምራች እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ቃል በተገባበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ነው ብለዋል። በማከልም፣ በጥራት መንደር የሚገኙ ከኃላፊ እስከ ፈጻሚ ያሉ ሠራተኞች የሕዝብ አገልጋይነታቸውን በመገንዘብ በመደመር እሳቤ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎችን በብቃት፣ በታማኝነትና በቅንነት አስቀጥለው ለውጤት ማብቃት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

 

በበዓሉ አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የተዘመረ ሲሆን፣ ሠንደቅ ዓላማውን በክብር የመስቀል ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ በጥራት መንደር የሚገኙ የአምስቱ ተቋማት የሥራ አመራር አባላት እና ሠራተኞች በጋራ ተሳትፈዋል።