«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ (ኢተምድ)

=================

«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ በፓናሊስትነት የተሳተፉበት ሀገራዊ የጥራት የፓናል ውይይት በጥራት መንደር ተካሄደ።

በተቋማትና በሕብረተሰቡ ዘንድ ስለ ጥራት ያለው ግንዛቤ እያደገ ቢመጣም፣ ጥራትን የዘወትር ባህል ከማድረግ አንጻር አሁንም ክፍተቶች እንደሚታዩ በውይይቱ ላይ ተገልጿል። እነዚህን ክፍተቶች ለመሻገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለጥራት ባህል ግንባታ ዋና ዳይሬክተሯ ካነሷቸው ዋና ዋና የመፍትሔ ነጥቦች መካከል ጥራትን የተቆጣጣሪ አካላት የቁጥጥር ማዕቀፎች ለማለፍ ብቻ ከመጠቀም፤በየቀኑ የአገልግሎት አሰጣጥና አሰራር ውስጥ ጥራትን እንደ ባህል መወሰድ እንደሚገባ አብራርተዋል።

በተጨማሪም የጥራት ጉድለት ሲያጋጥም ሠራተኞችን ከመውቀስ ይልቅ ጥፋቱ እንዳይደገም የሚያደርግ የአሰራር ሂደት ማሻሻያ መተግበር፣ ጥራትን በድህረ-ቁጥጥር ለማረጋገጥ ከመሞከር ይልቅ ስህተቶችና ጉድለቶች እንዳይከሰቱ የሚያስቀር የቅድመ-መከላከል አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

አክለውም ጥራትን በጥራት ተቆጣጣሪ አካላትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቻ የሚረጋገጥ ሳይሆን የመላው ህብረተሰብ የጋራ ኃላፊነት ማድረግ፣ ከዘልማድ አሰራር በመውጣት በጥራት መስፈርቶችና በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን መስጠት እንዲሁም ቀጣይነት ባለው የማሻሻያ ሥራ ላይ ማተኮር ወሳኝ መሆናቸውን ለመድረኩ ተሳታፊዎች አብራርተዋል።