ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።

ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም

ወላይታ (ኢተምድ)

=================

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት(ኢተምድ) የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ለሚያስገነባው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም አካሄደ። ኢተምድ ህንፃውን በባለቤትነት አስገንብቶ ለከተማው አስተዳደር የሚያስረክብ ሲሆን፣ ትምህርት ቤቱም አምራችና ብቁ ዜጋ የሚፈራበት ተቋም እንደሚሆን ተገልጿል። በተጨማሪም ድርጅቱ ለ150 የአረካ ከተማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

 

መሠረተ ድንጋዩንም የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ እና የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕ ሳሙኤል ተሰማ በአንድነት አስቀምጠዋል።

 

በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ፣የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕ ሳሙኤል ተሰማ፣ የኢተምድ የሥራ አመራር አባላት፣ የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማሬ ቦታ፣ የአረካ ከተማ ከንቲባ ኢ/ር ጥበቡ ሳሙኤል፣ የአረካ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዛራን ጨምሮ የከተማው አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።