ስራ አመራር ስርዓት ሰርተፍኬሽን (ISO/IEC 17021)
ኢተምድ የሥራ አመራር ስርዓት ሰርተፍኬሽን አገልግሎት በዓለም አቀፍ ደረጃዎች መሰረት ይሰጣል፡፡
የስራ አመራር ስርዓት ሰርተፍኬሽን ማለት አንድ ድርጅት የሚያከናውናቸውን ተግባራት፣ የምርቶቹንና የአገልግሎቶቹን የስራ ሂደት የሚመራበት አግባብነት ካላቸው የድርጅቱ ፖሊሲና ከዓለም አቀፍ የስራ አመራር ሥርዓት ጋር የተጣጣመ ስርዓት መተግበሩን በመገምገም ተፈላጊ ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ በገለልተኛ ወገን የሚሰጥ የስራ አመራር ስርዓት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ነው፡፡
በኢተምድ የስራ አመራር ስርዓት ሰርተፊኬሽን የሚሰጥባቸው መስኮች (ISO/IEC 17021)
- የጥራት ስራ አመራር ስርዓት (ISO9001:2015)
- የአካባቢ ስራ አመራር ስርዓት (ISO14001:2015)
- የስራ ቦታ ጤና እና ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት (ISO45001:2018)
- የምግብ ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት (ISO22000)
ኢተምድ በISO 9001፡2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት በ13 የተለያዩ መስኮች ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የሰርቲፊኬሽን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
እነዚህም መስኮች፡
ግብርና፣የደን ልማት፣አሳ እርባታ፤የምግብ ምርቶች፣መጠጦችና ትንባሆ፣
ጨርቅና የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች፤ቆዳና የቆዳ ምርቶች
ማተሚያ ድርጅቶች፣ኬሚካልና የኬሚካል ምርቶች፣ ጎማና ፕላስቲክ ምርቶች፤ ብሎኬት፣ሲሚንቶ፣አሸዋ የመሳሰሉት
ብረታ ብረት፤የግንባታ ምርቶች፣ ምህንድስናና የዲዛይን ቢሮዎች፤ህዝብ አስተዳደር ትምህርት ናቸው፡፡