የኢተምድ የምግብ እና የመጠጥ ፍተሻ ላብራቶር ከ90 በላይ ለሚሆኑ የምግብና የመጠጥ ምርቶች በ800 የፍተሻ ባህሪያቶች የፍተሻ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ እነዚህ የምግብና መጠጥ ምርቶች ከምርት ደህንነት እና ጥራት አንፃር በተቀመጠላቸው የደረጃ መስፈርት መሰረት ይፈተሻሉ፡፡
በኢተምድ የምግብ እና መጠጥ ፍተሻ ላብራቶር የሚፈተሹ ምርቶች እና የፍተሻ ባህሪያት በጥቂቱ
ምርቶች
- የምግብ ዘይት
- ውሃ
- ለስላሳ እና የአልኮል መጠጦች
- የገበታ ጨው
- የጁስ ምርቶች
- ዳቦ ና እንጀራ
- ጣፋጮች
- የቲማቲም ድልህ
- የህፃናት አልሚ ምግቦች
- ዱቄት ወዘተ የፍተሻ ባህሪያት
1.የቫይታሚን አይነት / Vitamin types
2.የምርት ይዘት/ Composition
3.የምርት ግብዓት አይነት/Ingredients
4.የፈንገስ ዝርያዎች/ Mycotoxins (Aflatoxin,Ochratoxin …etc)
5.የስኳር ዓይነቶች /Sugar profile