የምርት ሰርተፍኬሽን (ISO/IEC 17065)
የምርት ሰርተፍኬሽን ማለት ምርቶች የተጠቀሱ ተፈላጊ/ተጠባቂ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ለማሳየት በገለልተኛ ወገን የሚሰጥ የምርት ጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ነው፡፡ ኢተምድ በዓለም አቀፍ አሰራር ስርዓት (ISO/IEC 17065 መሰረት በዘጠኝ የምርት አይነቶች እውቅና ያለው የምርት ሰርተፊኬሽን አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡
በኢተምድ የምርት ጥራት ሰርተፍኬሽን የሚሰጥባቸው መስኮች
- የምግብ ምርቶች፣
- የኬሚካልና ኬሚካል ምህንድስና ምርቶች፣
- የጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ምርቶች
- የግንባታ ግብዓት ምርቶች፣
- የኤሌክትሪክ ምርቶች፣
- የግብርና ምርቶች እና ግብዓቶች ወዘተ