ኢተመድ የጥራት ቀን መፅሄት የዓለም የጥራት ቀን የምርቶችና አገልግሎቶች ጥራት፣ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓትና ሂደት በሰውልጆች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የሚያስከትለውን ለውጥና እድገት አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ቀን ነው፡፡ የዓለም የጥራት ቀን ጥራት በአንድ ሀገር አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እድገትና ህልውና ላይ የሚኖረውን ድርሻ ለማስገንዘብ እ.ኤ.አ በ1990 ዓ.ም በተባበሩት መንግሥታት የተጀመረ ሲሆን የዓለም የጥራት ቀን በየዓመቱ ህዳር በገባ በሁለተኛው ሳምንት ሐሙስ ቀን ይከበራል፡፡ በዘንድሮ ዓመትምበዓለምአቀፍደረጃለ26ኛጊዜNovember 13, 2014 በሀገራችንደግሞለ3ኛ ጊዜ ህዳር 04 ቀን2007 ዓ.ም “ጥራቷን የጠበቀች ዓለም በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል ይከበራል… የኢተመድ መፅሄት ኢተምድ በዋነኝነት የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶችን ማለትም የላቦራቶር ፍተሻ ፣ የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በስሩ ከ180 በላይ ሰራተኞችን ይዞ በ7 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመላው ሀገሪቱ የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዓለምአቀፍ ተቀባይነትያለው የፍተሻ ላቦራቶር ፣ የኢንስፔክሽንና ሰርቲፊኬሽን የአሰራር ሥርዓቶችን በመተግበር ተዓማኒነት ያለው ፣ ገለልተኛ ፣ውጤታማ ፣ተደራሽና ቀልጣፋ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት በመስጠት ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት በመላው ሀገሪቱ እንዲኖር ማስቻልን ዓላማው አድርጎ የሚሰራ ድርጅት ነው…