የኢተምድ ሥራ መሪዎችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል!” በሚል መሪ ቃል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የቡናና የፍራፍሬ ችግኞችን ተከሉ።
ሐምሌ 27 ቀን 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
===================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት በጋራ “ተስፋን እንትከል!” በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ/ም በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ ሀገራዊ መርሃ ግብርን በመቀላቀል፤ በአዲስ አበባ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ዳርቻ ላይ የቡናና የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራተውን አኑሯል።
በዚህ ሀገራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በአካል ተገኝተው የቡና እና የፍራፍሬ ችግኞችን የተከሉ ሲሆን፤ ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለንግዱ ዘርፍ የጎላ ኢኮኖሚያዊ ትርጉም ያለው መሆኑን አብራርተዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፣ ዛሬ የተከልናቸው የቡናና የፍራፍሬ ችግኞች አካባቢን ከመንከባከብና ከማልማትም ባሻገር፤ የሀገራችንን የወጪ ንግድ አቅም ለማሳደግና የውጭ ምንዛሬ ግኝታችንን ከፍ ለማድረግ የነገ ብሩህ ተስፋዎቻችን ናቸው ብለዋል።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ በበኩላቸው የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች አድገው ለታለመለቸው ዓላማ እንዲውሉ ለማድረግና የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራማችን ውጤታማ ለማድረግ ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።




Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡