ኢተምድ በ19ኛው የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት (AFRIMETS) ጠቅላላ ጉባኤ ተሳተፈ።

ኢተምድ በ19ኛው የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት (AFRIMETS) ጠቅላላ ጉባኤ እየተሳተፈ ይገኛል።
ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስኬታማ እንዲሆን ከታሪፍ ቅነሳ ጎን ለጎን ተዓማኒ የጥራት መሠረተ ልማት መዘርጋት ወሳኝ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ይህንን ያመለከቱት በኢትዮጵያ ሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በጥራት መንደር “ሥነ-ልክ ለዲጂታል ሽግግር፡ ተዓማኒ ልኬቶች ለአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው 19ኛው የአፍሪካ ሥነ-ልክ ድርጅት (AFRIMETS) ጠቅላላ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
በዚህ አህጉራዊ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ተሳታፊ በመሆን ከተለያዩ አባል ሀገራት ለተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች እና የቴክኒክ ኮሚቴ ባለሙያዎች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እያስተዋወቀ ይገኛል። በመጨረሻም የኢተምድ የሥራ ኃላፊዎች ከጉባኤው ተሳታፊዎች ጋር በመሆን በጥራት መንደር ግቢ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።