የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
ነሃሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
በኢትዮጵያ የውሃ መሠረተ- ልማት ግንባታ ላይ የሚውሉ የቴክኖሎጂ ግብአቶችና ምርቶች፣ በተለይም የኤች ዲ ፒ ኢ (HDPE) ቱቦዎች፣ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ያለመ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።
የውይይት መድረኩ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) እና በጣና ቁፋሮና ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ. ማህበር በጋራ የተዘጋጀ ነው።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ በመድረኩ ባስተላለፉት መልእክት፤ ደረጃቸውን የጠበቁ የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችና የኤች.ዲ.ፒ. ኢ (HDPE) ቱቦዎች ለሀገሪቱ ዘላቂ ኢኮኖሚ፣ ለሰው ልጅ ጤና እና ደህንነት ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አምራቾችና አገልግሎት ሰጪዎች ከጥሬ ዕቃ እስከ ምርት ያሉ ሂደቶች ብሄራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አክለውም ኢተምድ እውቅና ባላቸው 9 ላቦራቶሪዎች፣ በኢንስፔክሽንና በሰርቲፊኬሽን አገልግሎቶቹ ጥራትን ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆኑን ገልጸው፣ አምራቾች፣ ተቆጣጣሪዎችና ተጠቃሚዎች በጋራ በመስራት የጥራት ሰንሰለቱን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል። በመድረኩ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ማህበራት እንዲሁም አምራቾች ተሳትፈውበታል፡፡