ኢተምድ ከአምራች ድርጅቶችና ማህበራት ጋር የጋራ መድረክ አካሄደ፡፡
ሐምሌ 23 ቀን 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግና ኢተምድ የጨመራቸውን አዳዲስ አገልግሎቶች ለማስተዋወቅ እንዲሁም ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያካሂደውን መድረክ አካል የሆነው ከተለያዩ የኮንስትራክሽን ፣ የጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ፣ የሳሙና እና ዲተርጀንት እንዲሁም የኬሚካል አምራች ድርጅቶች እና ማህበራት ጋር የጋራ መድረክ አካሄደ።
የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ መድረኩን በንግግር የከፈቱ ሲሆን፣ ድርጅቱ በ2018 በጀት ዓመት የአገልግሎት ወሰኖችን ለማስፋትና ዓለም አቀፍ አሰራርን የተከተሉ የጥራት ማረጋገጫዎችን ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል።
በመድረኩም የአገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማዘመንና በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት ጥራቱን የጠበቀና ፈጣን አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችሉ ውይይቶች ተደርገዋል።
ድርጅቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች በዋና መ/ቤት ብቻ ተወስነው የነበሩ የፍተሻ አገልግሎቶችን በአዳማና በድሬዳዋ ላብራቶሪዎች በማደራጀት ወደ ክልል ቅርንጫፎች የማስፋት ሥራ መከናወኑና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን፤ በመድረኩም ስለ አጠቃላይ የድርጅቱ አሰራርና አዳዲስ የአገልግሎት ወሰኖች የሚያስተዋውቅ ገለፃና ማብራርያ ተደርጓል ።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም በዘመናዊ የፍተሻ መሣሪያዎች የተደራጀውን የኢተምድ ፍተሻ ላብራቶሪዎች በአካል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።



Shared post

Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡