ኢተምድ በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ገለፀ፡፡
ሰኔ 26 ቀን 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት በፍተሻ ላቦራቶሪ፣ በወጪ እና በሀገር ውስጥ የምርትና አገልግሎት ኢንስፔክሽን ፣ በምርትና ስራ አመራር ስርዓት ሰርተፍኬሽን እና የፈሳሽ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ታንከር ይዘት ካሊብሬሽን አጠቃላይ 36,343 አገልግሎቶች፣ 2,566,871 ሜ/ቶን የአፈር ማዳበርያ እና የተለያዩ የጅምላ ጭነት እንዲሁም በጅቡቲ ወደብ 19,227,332 ሊትር የምግብ ዘይት የኢንስፔክሽን አገልግሎቶች መሰጠቱን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የተስማሚነት ምዘናና የሥልጠና አገልግሎቶችን ለአምራቾች፣ ላኪዎች፣ አስመጪዎችና ተቆጣጣሪ አካላት እየሰጠ እንደሚገኝ ኢንጂነር መዓዛ አበራ አብራርተዋል። ተቋሙ ፍትሃዊ የንግድ ውድድር እንዲሰፍን፣ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ እንዲገነባ እንዲሁም የሸማቾች ጤና እና የአካባቢ ደህንነት እንዲጠበቅ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም ገልፀዋል


Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡