ኢተምድ ተጨማሪ አዲስ የአክሬዲቴሽን እውቅናዎችን አገኘ፡፡

ኢተምድ ተጨማሪ አዲስ የአክሬዲቴሽን እውቅናዎችን አገኘ፡፡
ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) የአገልግሎት ጥራቱንና ተዓማኒነቱን ይበልጥ የሚያሳድጉ ተጨማሪ አዳዲስ የዕውቅና ምስክር ወረቀቶችን ከኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት አገኘ። ኢተምድ እውቅናዎቹን ያገኘው በፍተሻ ላብራቶሪ እና በሰርቲፊኬሽን ዘርፎች በተለያዩ የወሰኖች ላይ ነው። እውቅናው የድርጅቱን የፍተሻና ሰርቲፊኬሽን አገልግሎት ተዓማኒነት በማሳደግ የሀገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ ለማሳለጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ይህ የእውቅና አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት የተከናወነው፣ የዓለም አቀፍ የአክሬዲቴሽን ቀን “አክሬዲቴሽን ለፈጠራ፣ እምነት እና ዘላቂነት” በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ተከብሮ በዋለበት መድረክ ላይ ነው።
በፍተሻ ላብራቶሪ (ISO/IEC 17025) በኬሚካልና ማዕድን፣ በኤሌክትሪካል፣ በሜካኒካል፣ በቆዳና ጨርቃ ጨርቅ በተለያዩ የፍተሻ ባህሪያት እንዲሁም በምርት ሰርቲፊኬሽን ISO/IEC 17065 በተለያዩ ምርቶች በተጨማሪም በሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬሽን ላይ ዓለም አቀፍ እውቅናዎችን አግኝቷል።