ኢተምድ ለጨርቃ ጨርቅና ቆዳ አምራቾች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ፡፡

ኢተምድ ለጨርቃ ጨርቅና ቆዳ አምራቾች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ፡፡
ሰኔ 03 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) ከአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ቢሮ ጋር በመተባበር ለተመረጡ የጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ አምራቾች በምርት ጥራትና በሥራ አመራር ሥርዓት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሄደ።
የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በዘርፉ የምርት ጥራትን ደረጃው ጠብቆ ማስቀጠል ስላለው ጠቀሜታና ድርጅቱ ስላለው ሚና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዕለቱ በተካሄደው ውይይት ኢተምድ የሚሰጣቸው የተለያዩ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች፣ የጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ አምራች ተቋማት የምርት ጥራትንና የሥራ አመራር ሥርዓትን በተሟላ ሁኔታ በተግባር ላይ ማዋል በሚችሉባቸው ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለጻና ውይይት ተደርጓል። ከግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ማጠናቀቂያ በኋላ የመድረኩ ተሳታፊዎች በዘመናዊ የፍተሻ መሣሪያዎች የተደራጀውን የኢተምድን የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ፍተሻ ላብራቶሪ በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል። ይህ ጉብኝት አምራቾች የላብራቶሪውን የቴክኖሎጂ አቅምና የፍተሻ ሂደቶች በተግባር እንዲያዩ እንዲሁም ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ከመላካቸው በፊት ስለሚደረጉ የጥራት ማረጋገጫ መንገዶች የተሻለ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ዕድል የፈጠረ ነበር