የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ከኢፌድሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዋና መ/ቤትና ተጠሪ ተቋማት በጋራ “ትውልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል 22ኛው የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከብሯል፡፡
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) “ትውልድ በስነ-ምግባር ተኮትኩቶና ታንጾ ሲያድግ ተቋማት ከሙስና የጸዱና ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ይሆናሉ” ብለዋል፡፡

ሙስና ከአስተሳሰብ እንደሚጀምር በመረዳት ከሙስና የጸዳች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አበይት የፀረ-ሙስና መርሆዎችን በተሟላ መልኩ መፈፀም እንደሚገባ አጽንኦት ሰጠተው ተናግረዋል።
አክለውም የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማጠናከር ግልጸኝነት ያለው የአሠራር ስርዓትን መዘርጋት እና ቴክኖሎጂን በአግባቡ በመጠቀም አሰራሮችን ፈጣንና ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሁሉም አመራሮችና ሰራተኞች ስነ-ምግባር የተላበሰና ከሌብነት የጸዳ ተቋም ለመፍጠር በትብብርና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።
በዚሁ መድረክ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር የሃብት ምዝገባ ሰነድ ርክክብ አድርገዋል።
በመጨረሻም ባለ 5 የአቋም መግለጫ በማስተላለፍ በዓሉ የተከበረ ሲሆን መላው ሰራተኛ ደግሞ በonline ሃብቱን በአጭር ጊዜ እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል፡፡

Related Posts
“ጥራት፡ በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል የዓለም የጥራት ሳምንት በጥራት መንደር ውስጥ የተዘጋጀውን የጥራት ኤክስፖ ተጠናቀቀ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተገኙበት አምስት ተቋማትን በአንድ ላይ በመያዝ የተደራጀው የጥራት መንደር አንደኛ ዓመት በዛሬው ዕለት በደማቅ መረሃ ግብር ተከብሯል ።
“ጥራት፡ በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል የዓለም የጥራት ሳምንት በጥራት መንደር ውስጥ የተዘጋጀውን የጥራት ኤክስፖ በክቡር የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ደ/ር ካሳሁን ጎፌ በይፋ ተከፈተ።