“ጥራት፡ በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል የዓለም የጥራት ሳምንት በጥራት መንደር ውስጥ የተዘጋጀውን የጥራት ኤክስፖ በክቡር የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ደ/ር ካሳሁን ጎፌ በይፋ ተከፈተ።

“ጥራት፡ በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል የዓለም የጥራት ሳምንት በጥራት መንደር ውስጥ የተዘጋጀውን የጥራት ኤክስፖ በክቡር የኢፌዲሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ደ/ር ካሳሁን ጎፌ በይፋ ተከፈተ።
ህዳር 11ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያደረጉ ሲሆን መንግስት ለጥራት የሰጠውን ልዩ ትክረት ድርጅቱ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት የመስጠት ዓቅሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭና ተወዳዳሪ ተቋም መሆን መቻሉን አብራርተዋል።
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የዓለም የጥራት ሳምንቱን በደረጉት የመክፈቻ ንግግር የዘንድሮው የጥራት ቀን የሚከበረው የኢፌድሪ መንግስት በጠራ እሳቤ ከምን ጊዜውም በላይ ለጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከ8.2 ቢሊዮን ብር በላይ መዋለ ንዋይ በመመደብ በአፍሪካ ቀዳሚ በዓለም ተወዳዳሪ የጥራት መንደር ገንብተን ባጠናቀቅንበት ማግስት ነው። ያለጥራት በየትኛውም መስክ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት አይታሰብም ብለዋል።
ኢንጂነር መዓዛ አበራ በበኩላቸው የሃገራችን የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ለማፋጠን የባለድርሻ አካላት እና አምራቾች እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጥራቱ የተጠበቀና በደረጃዎች ለይ የተገለፁትን መስፈርቶች አሟልተው ለተጠቃሚዎች ማድረስ ይጠበቅባችዋል ብለዋል።
የዓለም የጥራት ሳምንትን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት ማረጋገጫ ያገኙ ከ150 በላይ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በማሳተፍ በጥራት መንደር ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሕዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም የምከበር ይሆናል። በዚህ የጥራት ኤክስፖ የተለያዩ የምርት ዓይነቶች በፋብሪካ ዋጋ ይሸጣሉ።