የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተገኙበት አምስት ተቋማትን በአንድ ላይ በመያዝ የተደራጀው የጥራት መንደር አንደኛ ዓመት በዛሬው ዕለት በደማቅ መረሃ ግብር ተከብሯል ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተገኙበት አምስት ተቋማትን በአንድ ላይ በመያዝ የተደራጀው የጥራት መንደር አንደኛ ዓመት በዛሬው ዕለት በደማቅ መረሃ ግብር ተከብሯል ።
ህዳር 13-2018 ዓ.ም – (ኢተምድ)
====================
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት “ይህ ዓለም አቀፍ የጥራት ስታንደርድን ጠብቆ የተገነባው የጥራት መንደራችን የዛሬ አስር ዓመት ገደማ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አብይ አህመድ (ዶ/ር) አርቆ አሳቢነት የተጀመረ ሲሆን ከበርካታ ዓመታት መጓተት በኋላ በከፍተኛ ትጋትና ዲሲፕሊን ስራው ተጠናቆ ህዳር 14 ቀን በ2017 ዓ.ም. በክቡር በጠቅላይ ሚኒስትራችን ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
እንደ ስሙ የጥራት ምልክት የሆነውና በተሳለጠ አደረጃጀት የተዋቀረው የጥራት መንደራችን በባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ጥራትን ማስጠበቅና ለሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ንግድ ትስስራችን ትልቅ አቅም ፈጥሮልናል ብለዋል።
በቀጣይም አሁን ያለውን ፋሲሊቲ በማስጠበቅና ወደፊትም ዘመንን የዋጀ እንዲሆን የፈጠራ አቅማችንን በማጎልበት የበለጠ በማላቅ የማያቋርጥ ዕድገት የምናረጋግጥ ይሆናል በማለት ክቡር ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር እና የጥራት መንደር የበላይ ጠባቂ ኢንጂነር መዓዛ አበራ የምስጋና እና የፕሮግራሙ የመጠቃለያ ንግግር አድረገዋል።