የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ ያስገነባውን ህንፃ እና የፍተሻ ላብራቶሪ በይፋ አስመረቀ። ጥር 16/2018 ዓ/ም አዳማ (ኢተምድ)

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ ያስገነባውን ህንፃ እና የፍተሻ ላብራቶሪ በይፋ አስመረቀ።
ጥር 16/2018 ዓ/ም
አዳማ (ኢተምድ)

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በአዳማ ከተማ ያስገነባውን ሀንፃ እና የፍተሻ ላብራቶሪ በይፋ አስመረቀ፡፡

የጥራት ማረጋገጫ የሚሰጥበትን ማእከል መረቀው የከፈቱት የኢፌዲሪ ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ሲሆኑ የጥራት ተቋማት የንግዱን ዘርፍ ሃገራዊ የማስፈጸም አቅምና በወጪ ንግድ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን በጽኑ መሰረት ላይ ለማስቀመጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው በቀጣይም የጥራት መንደራችንን ፈለግ ተከትለን መሰል የጥራት መሰረተ ልማቶችን በመላው የሃገራችን ክፍሎች በማስፋፋት ጥራትን •ለማረጋገጥ በትጋት እንሰራለን ብለዋል።
የኢፌዲሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም የኢተምድ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ክብር አቶ እንዳለው መኮንን በአደረጉት ንግግር በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዘመናዊ ህንፃና የፍተሻ ላቦራቶሪ ተገንብቶ ለምረቃ እንዲበቃ ክትትል ለአደረጉ ለኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ፣ ለኢተምድ ቦርድ አባላት፣ የማነጅመንት አባላት፣ እንዲሁም መላው የኢተምድ ሰራተኞች እንኳን ደስ ያላቸው ብለዋል። ኢተምድ ይህን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መክፈቱ የአገልግሎት ወሰን በማስፋት መንግስት የሀብረተሰቡን ጤንነትና ደህንነት እንዲረጋገጥ ለድርጅቱ በሰጠው ስትራቴጂክ ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን ማሳያ እንደሆነ ገልፀዋል።
የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎት ያስተዋወቁ ሲሆን ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶችም የእንኳን ደሀና መጠችው መልዕክት ኣስተለለፈዋል። ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጥራቱን ጠብቆ የተገነባ እና በዘመናዊ የፍተሻ ላቦራቶሪ መሳሪያ እንዲሁም በሰለጠኑ ባለሙያዎች የተደራጀ በመሆኑ በአዳማ ከተማና አካባቢ የሚገኙ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪዎች፣ አስመጪና ላኪዎች፣ የመንግስት ተቆጣጣሪ አካላት እና ሸማቾች እንዲጠቀሙበት ጥሪያቸውን አቀርበዋል፡