ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢተምድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢተምድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡

የካቲት 29 ቀን 2018ዓ.ም

አዲስ አበባ (ኢተምድ)

==================

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ጉብኝቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በድሬዳዋ አዲስ የፍተሻ ላቦራቶሪ አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የአሰራር ስርዓትን በመከተል ለአምራቾች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ ለላኪዎች፣ ለአስመጪዎች፣ ለተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቶች፣ ለምርምር ተቋማትና ለሸማቹ ማህበረሰብ የምርትና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎትን እየሰጠ ነው ብለዋል፡፡

‎‎በድሬዳዋ አካባቢ ለሚገኙ አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ነፃ የንግድ ቀጣና እንዲሁም የደረቅ ወደብን መሰረት በማድረግ አዲስ የፍተሻ ላቦራቶሪ በማደራጀት አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረጉን ገልፀዋል። ተቋሙ በድሬዳዋ ከተማ ቀደም ብሎ ይሰጡ ከነበሩ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች በተጨማሪ በምግብ ዘይት፣ በነዳጅ ምርት፣ በተለያዩ የምግብ ምርቶች፣ ለማስዋቢያና የዲተርጀንት ምርቶች፣ ለኮንስትራክሽን ምርቶችና ግብዓቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ይህ የአገልግሎት ተደራሽነት መስፋፋት የኢትዮጵያን የጥራት መሰረተ ልማት ለማጠናከር እና የአገር ውስጥ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እንደ ትልቅ እርምጃ ይታያል ብለዋል።