የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሥራ እንቅስቃሴ ገመገሙ፡፡
የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
=================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሚሰጣቸውን የፍተሻ ላቦራቶሪ፣ የኢንስፔክሽንና የሰርተፊኬሽን አገልግሎቶች ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ የሀገራችን አከበቢዎችና ሀገራችን የምትጠቀምባቸው ወደቦች የአገልግሎት ፍላጎትን መሰረት በማድረግ አገልግሎት መስጫ ማእከላትን በመክፈትና በማደራጀት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በዚህ መሰረት በድሬዳዋ ከተማ ቀደም ብሎ ይሰጡ ከነበሩ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች በተጨማሪ በምግብ ዘይት፣ ፔትሮሌም ወይም የነዳጅ ምርት፣ የተለያዩ የምግብ ምርቶች እና የማስዋብያና የዲተርጀንት ምርቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የፍተሻ ላቦራቶሪ በማደራጀት አገልግሎቱን እያሰፋ ይገኛል።
በመሆኑም የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአካል ተገኝተው እየተደራጁ የሚገኙት አዳዲስ የፍተሻ ላቦራቶሪዎች ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር የስራ ግምገማ አድርገዋል።
በተጨማሪም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እየተደራጁ ያሉትን አዳዲስ አገልግሎቶች ለድሬዳዋ ምክትል ከንትባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ ለድሬዳዎ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊዎችና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የማስተዋወቅ ስራም ተሰርቷል።


Related Posts
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ ያስገነባውን ህንፃ እና የፍተሻ ላብራቶሪ በይፋ አስመረቀ። ጥር 16/2018 ዓ/ም አዳማ (ኢተምድ)
የኢተምድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀንን አከበረ፡፡ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ)
“ጥራት፡ በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል የዓለም የጥራት ሳምንት በጥራት መንደር ውስጥ የተዘጋጀውን የጥራት ኤክስፖ ተጠናቀቀ።