ኢተምድ ለደብረብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001 የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት ሰጠ።
ግንቦት 22 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለደብረብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001 የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት ሰጠ።
ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት የዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላቱን በተከናወነለት የኦዲት ሂደት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ሰርቲፊኬቱን ሊያገኝ ችሏል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ እንዲሁም ኢተምድ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን መንግስት ለጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘመናዊ የጥራት መንደር በመገንባትና አስፈላጊ የጥራት መፈተሻ መሳሪያዎችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም አስረድተዋል።



Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡