ኤሌክትሪካል ፍተሻ

የኢተምድ ኤሌክትሪካል ፍተሻ ላብራቶር 29 አይነት የኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ምርቶች በ141 የፍተሻ ባህሪያት የፍተሻ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ የኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከደህንነት፣ ከጥራት እና ሊሰጡት ከሚችሉት የአገልግሎት ብቃት አንፃር በተቀመጠላቸው የደረጃ መስፈርት መሰረት ይፈተሻሉ፡፡

በኢተምድ የኤሌክትሪካል ፍተሻ ላቦራቶር የሚፈተሹ ምርቶች  እና የፍተሻ ባህሪያት በጥቂቱ  

                 ምርቶች

  • የተለያዩ ባትሪ ድንጋይ፣      
  • ማብሪያና ማጥፊያ፣
  • የኤሌክትሪክ ገመዶች እና ኬብሎች፣
  • ሶኬት፣
  • የኤሌክትሪክ መስመር መቆጣጠሪያ (ብሬከር)፣
  • ኢንካንደስንትና ፍሎረሰንት አምፖል፣
  • ኃይል ቆጣቢ አምፖል፣
  • የተለያየ ፊቲንግ፣
  • በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ ምርቶች (ባትሪ፣ፓነል፣ ኢንቨርተር፣ ቻርጅ ኮንትሎረር) ወዘተ

   የፍተሻ ባህሪያት

  1. Conductor resistance
  2. Luminous Flux
  3. Power
  4. Normal operation
  5. Max. Application life hour
  6. Breaker Capacity
  7. open Circuit voltage
  8. Short circuit current etc