የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሥራ አመራሮችና ሰራተኞች በሰበታ ሀዋስ ወረዳ ሁለተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አከናወኑ፡፡

የኢተምድ የሥራ አመራር አባላት እና ሰራተኞች ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከሌሎች ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ሐምሌ 25ቀን 2015ዓ.ም በሰበታ ሀዋስ ወረዳ ደበል ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል፡፡ በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ የድርጅቱ የበላይ አመራሮች እንደሀገር የተያዘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ችግኝ መትከል ለትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ ተግባር እንደሆነ እና ለተተከለው ችግኝም ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ስራ መሆኑን መልእክት አስተላልፈዋል።