3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።

3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
ሐምሌ 15 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች በጥራት መንደር ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት ማረጋገጫ የፍተሻ ላቦራቶሪዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክትና ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
“Empowering Africa through trade and Investment Synergies” በሚል መሪ ቃል 3ኛው የአፍሪካ የንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ መካሄድ መጀመሩ ይታወቃል ።
የፎረሙ ተሳታፊዎች በሁለተኛው ቀን ውሎ በጥራት መንደር የሚገኘውን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለወጪና ገቢ ምርቶች እንዲሁም አገልግሎቶች የሚሰጣቸውን አጠቃላይ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል ።