የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
ሐምሌ 15 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አመራርና ሰራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡ ውይይቱን የድርጅቱን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ በንግግር የከፈቱት ሲሆን
እቅዱን ያቀረቡት የሰርቲፊኬሽንና የኢንስፔክሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አቤል አንበርብር ናቸው። የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ከ2018 ዕቅድ ጋር በንፅፅር የቀረበ ሲሆን እቅዱን ተፈፃሚ ለማድረግ የሁሉንም ርብርብ እንደሚጠይቅ ተመላክቷል።
በቀረበው ሀገራዊ እቅድ ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በተጨማሪም የድርጅቱን ዕቅድ ከሀገራዊ የልማት ዕቅድ ጋር በማቀናጀት ቀርቧል፡፡
በመጨረሻም የተለያዩ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ ፕሮግራሙን አጠቃለዋል።