
የኢተምድ ሥራ መሪዎችና ሠራተኞች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገሙ ፡፡
ሐምሌ 8 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት በፍተሻ ላቦራቶሪ፣ በወጪ እና በሀገር ውስጥ ኢንስፔክሽን, በሰርተፍኬሽን እና የፈሳሽ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ታንከር ይዘት ካሊብሬሽን አጠቃላይ 31,298 አገልግሎቶች እንዲሁም በጅቡቲ ወደብ 2,089,951 ሜ/ቶን የጅምላ ጭነት እና 43,708,931 ሊትር የምግብ ዘይት ኢንስፔክሽን አገልግሎቶችን መሰጠታቸውን የድርጅቱ ሰራተኞችና የስራ መሪዎች ገምግሟል፡፡
በጋራ ግምገማ መድረኩ የድርጅቱ ሰራተኞችና ስራ መሪዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት እጅግ ከፍተኛ ውጤት የተገኘበት በጀት ዓመት መሆኑን ገምግሟል፡፡ በግምገማው መድረክ ለ2018 በጀት ዓመት ድርጅቱ አገልግሎት የመስጠት አቅሙን በማሳደግና የአገልግሎት ወሰኑን በማስፋት የድርጅቱን የውስጥ አሰራር በማጠናከር፣የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሁም ተአማኒ በማድረግ ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ ተልእኮውን በላቀ ሁኔታ መፈፀም የሚያስችል ዝግጅቶች የተደረጉ መሆናቸውን ሰራተኞቹና የስራ መሪዎቹን ባደረጉት የጋራ ግምገማ አረጋግጧል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ላይ ጉልህ ሚናን ለመጫወት ዓለም አቀፍ እውቅናና ተቀባይነት ያለው የተስማሚነት ምዘና እና የሥልጠና አገልግሎትን ለአምራቾች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ለላኪዎች፣ለአስመጪዎች እና ለተቆጣጣሪ አካላት በመስጠት ፍትሃዊ የንግድ ውድድር በማስፈን ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ እንዲገነባ በመደገፍ የሸማቾችን ጤና እና የአካባቢ ደህንነትን የመጠበቅ ተልዕኮውን በተግባር ማሳየት የቻለ ተቋም መሆኑንም አረጋግጧል።
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።