
ኢተምድ ለአቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዳስትሪ እና ለ ኒው ፍላወር አጠቃላይ ንግድ ኀ/የተ/የግ/ማ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡
ሐምሌ 08 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለአቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዳስትሪ እና ለኒው ፍላወር አጠቃላይ ንግድ ኀ/የተ/የግ/ማ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ISO 9001 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡ ድርጅቶቹ ለጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት የተቀመጡ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላታቸውን በተከናወነላቸው የኦዲት ሂደት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘታቸው ሰርቲፊኬቱን ሊያገኙ ችሏል።
በሰርቲፊኬት ርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ኢንጂነር መዓዛ አበራ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የእንኳን ደስያላችሁ መልእክት በማስተላለፍ ኢተምድ የሚሰጣቸውን የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡ እንዲሁም በሌሎች የተስማሚነት ምዘና የሥራ መስኮች በጋራ ለመስራት የኢተምድን ዝግጁነት ገልፀውላቸዋል፡፡ የሁለቱም ሰርቲፊኬት ያገኙ ድርጅቶች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው በተሰማሩባቸው የስራ መስኮች በሃገር ውስጥ ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳደሪና ተመራጭ ለመሆን ያስቀመጥነውን ግብ ለማሳካት ድርጅታችን ይህንን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት መተግበሩ በጣም አስፈላጊና ጊዜው የሚጠይቀው መሆኑን ጠቅሰው ሌሎች የሥራ አመራር ሥርዓት ዘርፎችና በምርት ጥራት ዙርያም በተቀናጀ ሁኔታ ለመተግበር የድርጅታቸው ፍላጎት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ሰርቲፊኬቱን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ ለድርጅቶቹን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አስረክበዋል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።