ኢተምድ ለኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሁለት የሥራ አመራር ሥርዓት ዘርፍ ሰርቲፊኬት ሰጠ።

ኢተምድ ለኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሁለት የሥራ አመራር ሥርዓት ዘርፍ ሰርቲፊኬት ሰጠ።
ሰኔ 27 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (ISO 14001) የአካበቢ ሥራ አመራር ሥርዓት እና (ISO 45001) የሥራ ቦታ ጤና እና ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት ሰጠ፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለሥራ አመራር ሥርዓቶቹ የተቀመጡ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላቱን በተከናወነለት ኦዲት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ሰርቲፊኬቱን ሊያገኝ ችሏል።
በሰርተፊኬት ርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት በማስተላለፍ ለኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸናፊ ዳባ ሰርተፊኬቱን አስረክበዋል፡፡