ኢተምድ በዓለም አቀፉ የጤና ኢኖቬሽንና ጥራት አውደ ርዕይ ተሳተፈ፡፡

ኢተምድ በዓለም አቀፉ የጤና ኢኖቬሽንና ጥራት አውደ ርዕይ ተሳተፈ፡፡
ሰኔ19 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
======================
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽንና ጥራት ጉባኤ “ኢኖቬሽን ለሁለንተናዊ የጤና ሽፋን” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው የጉባኤውን ዓላማ ሲገልፁ በጤናው ዘርፍ ያሉ ፈጠራዎችን፣ የአገልግሎት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚረዱ ሃሳቦች ላይ ትኩረቱን በማድረግ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያላትን ተሞክሮ የምታካፍልበትና ከሌሎች ሀገራት ልምድ የምትለዋወጥበት ትልቅ መድረክ ነው ብለዋል።
በጉባኤው ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮች፣ ተመራማሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ እና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በጉባኤው ላይ ከ46 በላይ የሚሆኑ ዓለም አቀፍ ኢኖቬተሮች አውደ ርዕይ እያቀርቡ የሚገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅትም በዚሁ አውደ ርዕይ በመሳተፍ የጤናውን ዘርፍ ጥራት ከማስጠበቅ ጋር በተገናኘ እየሰጣቸው የሚገኘውን አገልግሎቶች ለጉባኤው ተሳታፊዎች እና ለኤግዚቢተሮች የማስተዋወቅና ግንዛቤ የመፍጠር ሥራን እየሠራ ይገኛል፡፡