
ኢተምድ ለሁለት ድርጅቶች የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።
ሰኔ 17 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለሳብያን ቤዝ ሜታል ኢንጂኔሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ (ISO 9001 Quality Management system) የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት እንዲሁም ለአለማየሁ ንጉሴ ሜታል ፓኬጂንግ (ISO 9001 Quality Management system) የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓትና (ISO 14001 Environment Management System) የአከባቢ ስራ አመራር ስርዓት ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላታቸውን በተከናወነላቸው የኦዲት ሂደት ተገምግሞ የተሰጣቸው ሲሆን ሰርቲፊኬቱን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ ለድርጅቶቹ የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል፡፡
በሰርቲፊኬቱ ርክክብ ወቅት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂኔር መአዛ አበራ ዓለም አቀፍ የስራ አመራር ስርዓት ሰርቲፊኬት ማግኘታቹ ለሚትሰጡት አገልግሎት ሆነ ለሚታመርቱት ምርት በሀገር ውስጥና በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲትሆኑ አስቻይ መሆኑን አብራርቷል ። አክለውም የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለድርጅቶቹ ተወካዮች ሰፊ ገለፃ ያደረጉላቸው ሲሆን በመጨረሻም የእንኳን ደስአላችሁ መልእክትም አስተላልፈዋል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።