
ኢተምድ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው 5ኛው የተመራቂ ተማሪዎች የሥራ አውደ ርዕይ ተሳተፈ፡፡
ሰኔ12 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው የ2017ዓ.ም የተመራቂ ተማሪዎች የሥራ አውደ ርዕይ በመሳተፍ ድርጅቱ የሚሰጣቸውን የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች፣ በድርጅቱ ለመቀጠር ተፈላጊ መስፈርቶች፣ድርጅቱ የሚፈልጋቸውን የትምህርት መስኮች፣ ከተመራቂ ተማሪዎች ተጠባቂ ክህሎቶች እና ድርጅቱ የሠራተኛ ቅጥር የሚፈፅምበትን አካሄድ በሚመለከት አውደ-ርዕዩን ለተሳተፉ ተመራቂ ተማሪዎች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ 5ኛውን የሥራ አውደ ርዕይ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተወካይ ክብርት ወ/ሮ ወርቅነሽ ዮሃንስ እና ዶ/ር ደረጀ እንግዳ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሪቫን በመቁረጥ መርቀው ከፍተውታል፡፡
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ የሚያዘጋጀው ይህ የሥራ አውደርዕይ ከ40 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶች የተሳተፉበት ሲሆን ተመራቂ ተማሪዎች ቀጣሪዎቻቸውን እንዲያውቁ ቀጣሪ ድርጅቶች ደግሞ ተወዳዳሪ እና ብቃት ያላቸው ምሩቃንን ለማግኘት እድል የሚፈጥር ነው፡፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅትም በተለያዩ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ ዘርፎች የሰለጠነ ሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ከዩኒቨርስቲው ጋር በትብብር በመስራት በተለያዩ ጊዜያት ተማሪዎቹን በመስክ ላይ ልምምድ እና የሥራ ላይ ስልጠና በመስጠት ተማሪዎቹን በማብቃት ረገድ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።