የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች በኢተምድ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች በኢተምድ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡
ሰኔ 06 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
===============
የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተቀናጀ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ተግባራዊነትና ዘላቂነት ፕሮጀክት (OS-IAIP) ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የላቦራቶሪ አደረጃጀትን በተመለከተ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያለመ የሥራ ጉብኝት በዛሬው እለት በኢተምድ አካሂደዋል፡፡
በጉብኝቱ የፕሮጀክቱ ስትሪንግ ኮሚቴ አባላትና የኮርፖሬሽኑ የበላይ የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ ኢተምድ የሚሰጣቸውን የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች በተመለከተ ገለፃ አቅርበውላቸዋል፡፡ በቀጣይም በጋራ ለመስራት የኢተምድን ዝግጁነት ገልፀውላቸዋል፡፡
የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ተግባራዊነት እና ዘላቂነት ፕሮጀክት በሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና በጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ (AICS) ትብብር በምግብ ደህንነት፣ጥራት እና ትሬሰብሊቲ በማረጋገጥ በሁሉም ደረጃ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን በማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ፕሮጀክት ሲሆን በዚህ ዘርፍ ኮርፖሬሽኑ እና ኢተምድ በጋራ ሊሰሩዋቸው የሚችሉ ሥራዎችን በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል፡፡