
ኢተምድ ከደብረብርሃን ዪኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ግንቦት 28 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
===============
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት እና የደብረብርሃን ዪኒቨርሲቲ በጥናትና ምርምር፣ በአቅም ግንባታ ስልጠና፣ በሀብት መጋራት፣ የጋራ ፕሮጀክቶችን በማጎልበት ተቋማዊ አቅምን በማሳደግ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በተስማሚነት ምዘና የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች ዘርፍ በትብብር መስራት የሚያስችላቸው የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል። የመግባቢያ ስምምነቱን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ እና የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ(ዶ/ር) ፈርመዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በምርምር ፕሮጀክቶች፣በአቅም ግንባታ ዘርፍ፣ የሀገር ሃብት የሆኑ መሳሪያዎችን በትብብር በጋራ በመጠቀም ተቋማቱ ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የሚችሉበት አቅምን በመፍጠር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑን የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ገልጸዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ለሚከተለው የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደረገና ተግባር ተኮር የትምህርት ሥርዓት ከኢተምድ ጋር የተደረገው ስምምነት ቁልፍ የአጋርነት ስምምነት እንደሆነ በመግለፅ የዩኒቨርሲቲውን መምህራንና ሌሎች ባለሙያዎች አቅም ለመገንባት፣ተማሪዎች የተግባር ልምምድ ለማድረግ፣ እና በጥናትና ምርምር ዘርፍ አብሮ ለመስራት እንደሚያግዘው ገልጸው ከኢተምድ ጋር ያላቸውን አብሮነትም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ ስምምነቱ የታለመለትን ግብ እንዲመታ ከሁለቱም ተቋማት ቴክኒካል ቡድን በማቋቋም ቀጣይ ውጤታማ ሥራዎችን ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
Related Posts
የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች በኢተምድ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡
ኢተምድ ለደብረብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001 የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት ሰጠ።
ኢተምድ ለላሜ ዴይሪ ኃ/የተ/የግ/ማ (ሾላ ወተት) የISO 14001 እና የISO 45001 የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት ሰጠ።