
ኢተምድ ለላሜ ዴይሪ ኃ/የተ/የግ/ማ (ሾላ ወተት) የISO 14001 እና የISO 45001 የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት ሰጠ።
ግንቦት 19 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለላሜ ዴይሪ ኃ/የተ/የግ/ማ (ሾላ ወተት) የ (ISO 14001) የአካባቢ ሥራ አመራር ሥርዓት እና የ (ISO 45001) የሥራ ቦታ ጤና እና ደህንነት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርቲፊኬት ሰጠ።
ላሜ ዴይሪ ኃ/የተ/የግ/ማ (ሾላ ወተት) የሥራ አመራር ሥርዓቶቹንን የዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ማሟላቱን በተከናወነለት የኦዲት ሂደት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ሰርቲፊኬቱን ሊያገኝ ችሏል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል በተጨማሪም ኢተምድ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን መንግስት ለጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘመናዊ የጥራት መንደር በመገንባትና አስፈላጊ የጥራት መፈተሻ መሳሪያዎችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ለድርጅቱ ተወካዮች አስረድተዋል።
Related Posts
3ኛው የአፍሪካ ንግድና ኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢተምድ ላቦራቶሪዎችን ጎበኙ።
የኢተምድ አመራርና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የኢተምድ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።