ኢተምድ ለካዲስኮ ቀለምና ማጣበቂያ ኢንዱስትሪ አ.ማ (ISO 45001) የሥራ ቦታ ጤና እና ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።

ግንቦት 14 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
===============
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለካዲስኮ ቀለምና ማጣበቂያ ኢንዱስትሪ አ.ማ የሥራ ቦታ ጤና እና ደህንነት ሥራ አመራር ሥርዓት (ISO 45001) ሰርተፊኬት ሰጠ።
አክስዮን ማህበሩ ሰርተፍኬቱን ያገኘው ለሥራ አመራር ሥርዓት የተቀመጡ ዓለም አቀፍ መመዘኛ መስፈርቶችን ማሟላቱን ኢተምድ ባካሄደው የኦዲት ግምገማ በመረጋገጡ ነው። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ ለአክስዮን ማህበሩ የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት እና በቀጣይ በሌሎች የአገልግሎት ዓይነቶች በጋራ ለመስራት ኢተምድ ዝግጁ መሆኑን በመግለፅ ሰርተፊኬቱን ለአክስዮን ማህበሩ የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።