ኢተምድ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።

ግንቦት 07 ቀን 2017ዓ.ም

አዲስ አበባ (ኢተምድ)

===============

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የ (ISO 9001) የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ሰርተፍኬቱን ያገኘው ለሥራ አመራር ሥርዓቱ የተቀመጡ ዓለም አቀፍ መመዘኛ መስፈርቶችን ማሟላቱን ኢተምድ ባካሄደው የኦዲት ግምገማ በመረጋገጡ ነው።  የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ ለባለስልጣኑ የሥራ ኃላፊዎች የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት እና በቀጣይ በሌሎች የአገልግሎት ዓይነቶች በጋራ ለመስራት ኢተምድ ዝግጁ መሆኑን በመግለፅ ሰርተፊኬቱን ለባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብዱልበር ሸምሱ አስረክበዋል።