
ግንቦት 06 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
==================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) የሥራ ኃላፊዎች ከInternational Center of Insect Physiology and Ecology Ethiopia (ICIPE) ካንትሪ ዳይሬክተር ዶ/ር ታደለ ተፈራ ጋር የማር ምርት ጥራትን በማስጠበቅ ዙሪያ ተወያዩ፡፡ በማር ምርት ላይ የጥራት ፍተሻ አቅምን በሀገር ውስጥ በመገንባት ዘርፉን ለማሳደግ ያለመ ፕሮጀክት አካል የሆነው ይህ ውይይት ኢተምድ ቀድሞ በማር ምርት ላይ እየሰጣቸው የሚገኙ የፍተሻ፣ የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎቶችን ወደላቀ ደረጃ በማሸጋገር ዘርፉን ለመደገፍ ለማስቻል ባለሙያዎችን በማብቃት፣በፍተሻ ግብዓት አቅርቦት፣አሰራር ሥርዓትን በማሻሻል እና አገልግሎቱን በማስተዋወቅ መስኮች ለኢተምድ ድጋፍ በማድረግ ሥራዎችን በጋራ መስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ በወይይቱ ወቅት የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መአዛ አበራ ኢተምድ እየሠጣቸው የሚገኘውን የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
Related Posts
ኢተምድ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።
ኢተምድ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የ9 ወር የእቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡
ኢተምድ ለኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሀዋሳ ካምፖስ የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።