
ሚያዝያ 25 ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ (ኢተምድ)
====================
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለምርቶች እና አገልግሎቶች የላቦራቶር ፍተሻ፣ የኢንስፔክሽን እና የሰርተፊኬሽን አገልግሎቶችን አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋናው የድርጅቱ መ/ቤት በተጨማሪ 9 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች እና በጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመክፈትና በማደራጀት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ በጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአፈር ማዳበሪያ፣የስንዴ፣የዘይት እና ሌሎች ገቢ ወጪ ምርቶች ላይ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት በመስጠት ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት እንዲኖር በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማፋጠን ከመንግስት የተሰጠውን ተልእኮ እየተወጣ ይገኛል።
በተጨማሪም ድርጅቱ ተልእኮውን በብቃት ለመወጣት ያሰፋቸውን አዳዲስ የአገልግሎት ወሰኖችን በሚመለከት ለቅርንጫፍ ኃላፊዎችና ተወካዮች ስልጠና ተሰጥቷል። በበጀት ዓመቱ ቀጣይ ወራት ታቅደው ያልተሰሩ ሥራዎችን በማካተት እቅዱን ከባለድርሻ አካላትና ደንበኞቻችን ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በመዘርጋት፣ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት ፍላጎትን መዳሰስና በመለየት የኢተምድን አገልግሎት የተደራሽነት አድማስ ማስፋት ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ በግምገማው ማጠቃለያ ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
Related Posts
ኢተምድ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።
የኢተምድ የሥራ ኃላፊዎች ከICIPE የሥራ ኃላፊዎች ጋር የማር ምርት ጥራት ማስጠበቅን በተመለከተ ተወያዩ ።
ኢተምድ ለኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሀዋሳ ካምፖስ የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።