
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሀዋሳ ካምፖስ (ISO 9001፡2015) የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ሰጠ። ኢንስቲትዩቱ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላቱን በተከናወነለት የኦዲት ሂደት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ሰርቲፊኬቱን ሊያገኝ ችሏል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ የኢተምድ የሰርተፊኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ እንየው የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት እና ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን መንግስት ለጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘመናዊ የጥራት መንደር በመገንባትና አስፈላጊ የጥራት መገልገያ መሳሪያዎች በማሟላት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም አስረድተዋል።
Related Posts
ኢተምድ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።
የኢተምድ የሥራ ኃላፊዎች ከICIPE የሥራ ኃላፊዎች ጋር የማር ምርት ጥራት ማስጠበቅን በተመለከተ ተወያዩ ።
ኢተምድ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የ9 ወር የእቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡