
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለሸገር ዳቦና ዱቄት ፋብሪካ በአራት የስራ አመራር ስርዓት (ISO 9001) የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት፣ (ISO14001) የአካባቢ ስራ አመራር ስርዓት፣(ISO 45001) የስራ ቦታ ጤና እና ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት እና (ISO 22000) የምግብ ደህንነት ስራ አመራር ስርዓት የተቀናጀ የሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።
ድርጅቱ ሰርተፍኬቱን ያገኘው በአራቱም የሥራ አመራር ሥርዓት የተቀመጡ ዓለም አቀፍ መመዘኛ መስፈርቶችን ማሟላቱን ኢተምድ ባካሄደው የኦዲት ግምገማ በማረጋገጡ ነው። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ ለድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች የኢተምድ አገልግሎቶች ማብራርያና የእንዃን ደስአላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ሰርተፊኬቱን ለድርጅቱ ስራ ሃላፊዎች አስረክበዋል።


Related Posts
ኢተምድ ለሁለት ድርጅቶች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ሰጠ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡