በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የተመሩ የባለስልጣን መ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች በዘመናዊ የፍተሻ መሳሪያዎች የተደራጁትን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዘጠኝ የፍተሻ ላብራቶሪዎች ጎብኝተዋል፡፡ የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ ኢተምድ የህብረተሰቡንና የአካባቢን ጤና እና ደህንነት ለማስጠበቅ ድርጅቱ የሚሰጣቸውን የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች በተመለከተ ገለፃና ማብራሪያ አድርገውላቸዋል፡፡
ጉብኝቱ እንደ ሀገር ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎትን በማቅረብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆንና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን ለማረጋገጥ ከጥራት አንፃር በድርጅቱ አገልግሎቶች ዙሪያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ግንዛቤ ለማሳደግ ዘርፉ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ማድረግንና ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠርን አላማው ያደረገ ነው፡፡



Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡