የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች “ቀጣናዊ ትስስር እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለንግድ ዘርፍ እድገት “በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በጥራት መንደር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
በዚህ የግምገማ መድረክ ኢተምድ በ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በፍተሻ ላብራቶሪ፣በወጪና ሀገር ውስጥ ምርት ኢንስፔክሽንና በሠርተፊኬሽን 23,636 አገልግሎቶችን እና በጁቡቲ ወደብ 1,403,415.45 ሜ/ቶን የአፈር ማዳበሪያና የተለያዩ የጅምላ ጭነት እንዲሁም 29,712,080 ሊትር የምግብ ዘይት ኢንስፔክሽን አገልግሎቶች በመስጠት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት እንዲኖር እና በጥራት ላይ የተመሰረተ ፍትሃዊ የግብይት ሥርዓት እንዲኖር የበኩሉን ድርሻ መወጣት መቻሉን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ ገለፃና ማብራርያ ሰጥተዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በመድረኩ ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር ባለፋት ዘጠኝ ወራት በትብብርና በቅንጅት በመሰራቱ በንግዱ ዘርፍ በርካታ ስኬቶችን ተጎናፅፈናል እነዚህን ስኬቶች ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገርና በጉድለት የታዩ ጉዳዮችም በቀሪ 3 ወራት በማካካስ የዘርፉን ውጤታማነትን ማጎልበት እንደሚገባ እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።