የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በሆኑት የተከበሩ ወ/ሮ አሻ ያህያ የተመራ የቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረጉ፡፡ የመስክ ምልከታው ዓላማ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መስሪያ ቤትና በተጠሪ ተቋማት ላይ ምልከታ በማድረግ ተቋማቱ በአዋጅ ወይም በደንብ የተሰጣቸውን ተልዕኮ እየተወጡ ስለመሆኑ ከሪፖርት ግምገማ ባሻገር በቦታው በአካል በመገኘት ለማረጋገጥ የክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ለማድረግ ነው፡፡
በመስከ ምልከታው ኢተምድ የሸማቾችንና የአካባቢን ጤናና ደህንነት በመጠበቅ በፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ የንግድ ውድድር ለማስፈን እና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ እንዲገነባ እየሰራቸው ስለሚገኙ የላብራቶር ፍተሻ፣ኢንስፔክሽንና ሰርቲፊኬሽን ሥራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በተጨማሪም የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂኔር መአዛ አበራ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት የ2017 በጀት ኣመት የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ገለፃ ያደረጉላቸው ሲሆን አባላቱም በመስክ ጉብኝታቸውና የቀረበላቸውን ገለፃ ደስተኞች መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በቀጣይ ትክረት ሊሰጣቸው የሚገቡ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ውይይቱን ተጠናቋል።