ኢተምድ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 7ኛ ዓመት አስመልክቶ ውይይት አካሄደ።

በኢትዮጵያ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም እውን የሆነውን ሀገራዊ ለውጥ 7ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ሰራተኞች የፓናል ውይይት አካሄዷል።
ውይቱ ‘ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!’ በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀውን የመነሻ ፅሁፍ ቀርቧል። በቀረበው ፅሁፍ መሰረት የድርጅቱ ሰራተኞችና የስራ መሪዎች ካስተላለፏቸው መልዕክቶች መካከልም፤ የጋራ ማንነት ግንባታ አስፈላጊነት፣ ህብረብሄራዊ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን ማጎልበት ፣ በድርጅታችን የሚንሰጣቸው አልግሎቶች ደረጀውን የጠበቀ መሆን እንደለበትና የህብረተሰቡንና የደንበኞቻችን እርካታን ከፍ በማድረግ ለውጡን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም የጋራ ግባችን የአፍሪካ ተምሳሌትነታችን፣ የመጋቢት ፍሬ የጋራ ትናንት የጋራ ዛሬ እና ቀጣዩ ጀግንነታችን ለኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነታችን የሚሉ መፈክሮችን በተለያዩ ባነሮች በማሳተም የጋራ እንዲሆኑ ተደርጓል።
በመጨረሻም ለውጡ እውን ከሆነ ወዲህ የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።