የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ (ISO 9001፡2015) የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ሰጠ። ኮሌጁ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላቱን በተከናወነለት የኦዲት ሂደት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ሰርቲፊኬቱን ሊያገኝ ችሏል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ ለኮሌጁ የበላይ ሥራ ኃላፊዎች ሰርቲፊኬቱን አስረክበዋል፡፡
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ የእንኳን ደስአላችሁ መልእክት እና ኢተምድ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ላይ ማብራርያ የሰጡ ሲሆን መንግስት ለጥራት ልዩ ትክረት በመስጠት ዘመናዊ የጥራት መንደር በመገንባትና አስፈላጊ የጥራት መገልገያ መሳርያዎች በማሟላት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም አስረድተዋል።



Related Posts
«በጥራት እንሻገር» በሚል መሪ ቃል የጥራት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢተምድ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የክረምት በጎ አድራጎት አገልግሎት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የውሃ መሠረተ- ልማት ግብአቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡