
ከመጋቢት 4‐8/2017 ዓ.ም “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 14ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርዒት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል ተከፍቷል፡፡ የንግድ ትርዒቱ በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና በኢፌዴሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን ለአምስት ተከታታይ ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ የንግድ ትርዒቱን የከፈቱት የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ ንግድ ትርዒቱ የሀገር ውስጥ ምርትና አገልግሎቶች የሚተዋወቁበትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ልምድ የሚለዋወጡበት እንደሚሆን ገልጸዋል።
በንግድ ትርኢቱ ኢተምድን ጨምሮ በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ከ200 መቶ በላይ የአገር ዉስጥ አምራቾች እና የዉጭ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅትም የምርትና አገልግሎቶችን ጥራትን የመጠበቅ እና የማስጠበቅ አስፈላጊነትን፣ጥራትን ለማስጠበቅ የሚሰጣቸውን የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶች፣ የድርጅቱን ተግባርና ኃላፊነት መሰረተ ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት ድርጅቱን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።
Related Posts
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ኢተምድን ጎበኙ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ፡፡
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢተምድ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡